መዝሙረ ዳዊት87

የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።

1መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤2ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።3የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ፥ በአንቺ የተከበረ ነገር ይባላል።4የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ፤ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።5ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ፤ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።6እግዚአብሔር ለሕዝቡ፥ በውስጥዋም ለተወለዱት አለቆችዋ በመጽሐፍ ይነግራቸዋል።7በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።

Copyright © 1962, 2003 United Bible Societies. Used for non-commercial purposes only; commercial use requires written permission from the Bible Society of Ethiopia.

https://www.wordproject.org/bibles/am/index.htm