መዝሙረ ዳዊት150

1ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑት፤ በኃይሉ ጠፈር አመስግኑት።2በችሎቱ አመስግኑት፤ በታላቅነቱ ብዛት አመስግኑት።3በመለከት ድምፅ አመስግኑት፤ በበገናና በመሰንቆ አመስግኑት።4በከበሮና በዘፈን አመስግኑት፤ በአውታርና በእምቢልታ አመስግኑት።5ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፤ እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት።6እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ።

Copyright © 1962, 2003 United Bible Societies. Used for non-commercial purposes only; commercial use requires written permission from the Bible Society of Ethiopia.

https://www.wordproject.org/bibles/am/index.htm