መዝሙረ ዳዊት133
የዳዊት የመዓርግ መዝሙር።
1ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።2ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።3በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።Copyright © 1962, 2003 United Bible Societies. Used for non-commercial purposes only; commercial use requires written permission from the Bible Society of Ethiopia.