መዝሙረ ዳዊት128
የመዓርግ መዝሙር።
1እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።2የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል።3ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።4እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።5እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።6የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።Copyright © 1962, 2003 United Bible Societies. Used for non-commercial purposes only; commercial use requires written permission from the Bible Society of Ethiopia.