መዝሙረ ዳዊት120

የመዓርግ መዝሙር።

1በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ሰማኝም።2ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።3ስለ ሽንገላ አንደበት ምንም ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?4እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።5መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።6ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች።7እኔ ሰላማዊ ነኝ፤ በተናገኋቸው ጊዜ ግን በከንቱ ተሰለፉብኝ።

Copyright © 1962, 2003 United Bible Societies. Used for non-commercial purposes only; commercial use requires written permission from the Bible Society of Ethiopia.

https://www.wordproject.org/bibles/am/index.htm